Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደስታ ሌዳሞ በኩታገጠም የለማ የቢራ ገብስን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ጤጥቻ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ የቢራ ገብስ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡

የጉብኝቱ ዓላማ የመኸር እርሻ ልማት እንቅስቃሴ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለመገምገም መሆኑም ተመላክቷል።

በዞኑ በመኸር እርሻው ከ29 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች መልማቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ከበደ ገልፀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩና የሥራ ሀላፊዎቹ በቀጣይም በዞኑ ሁላ ወረዳ በመኸር እርሻ የለማውን ሰብል ተዘዋውረው እንደሚመለከቱም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በሲዳማ ክልል በ2016/17 የመኸር አዝመራው በዋና ዋና ሰብሎች ከለማው ከ106 ሺህ 764 ሄክታር መሬት 12 ሚሊየን 500 ሺህ ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅም ተጠቁሟል፡፡

 

 

Exit mobile version