አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሴቶችን በግብርናው ዘርፍ ማሳተፍ ለተሻለ ምርታማነት ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለው የኢትዮጵያ ግብርና መሐንዲሶች ማህበር ገለጸ፡፡
በግብርናው ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት ያለመው የኢትዮጵያ ግብርና መሐንዲሶች ማህበር ዓመታዊ ኮንፈረንስ ተካሂዷል፡፡
የማህበሩ ፕሬዚዳንት ደበሌ ደበላ ÷ግብርናውን በሜካናይዜሽን ማዘመንና ሴቶችም እንዲሳተፉ መደረጉ ኢትዮጵያ እየተገበረችው ላለው ዘመናዊ የግብርና አካሄድ አጋዥ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ማህበሩ በሴት አርሶ አደሮች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግና በግብርናው ዘርፍ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት እየሰራ እደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በመድረኩ ግብርናውን በሜካናይዜሽን በመደገፍ ረገድ ክፍተቶች መኖራቸው የተነሳ ሲሆን÷ ሴቶችን ማብቃትና በዘርፉ ወደፊት እንዲመጡማድረግ ላይ ሊሰራ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
በሃይማኖት ወንድይራድ