አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለትምህርት ቤት አመራሮች የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና በዋቼሞ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ምሁራን በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ተገኝተዋል።
የትምህርት ሥርዓቱ በሰለጠነና የሙያ ብቃት ባለው የሰው ኃይል እንዲመራ ብሎም የተጠያቂነት ሥርዓትን ለማስፈን የትምህርት ቤት አመራር ሪፎርም መደረጉን ተከትሎ ነው ስልጠናው መሰጠት የጀመረው፡፡