Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቴሌ ብር ከ3 ነጥብ 25 ትሪሊየን ብር በላይ ዝውውር ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቴሌ ብር መተግበሪያ እስካሁን ከ3 ነጥብ 25 ትሪሊየን ብር በላይ ዝውውር መፈጸሙን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንዳሉት÷ ቴሌ ብር በኢትዮጵያ ዲጂታል የገንዘብ ልውውጥን ከማሳለጥ አንጻር ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው፡፡

መተግበሪያው ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑን ጠቁመው÷ በዚህም በበርካታ ደንበኞች ዘንድ ተመራጭ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የቴሌ ብር ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር ከ51 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ መድረሱን ገልጸው፤ መተግበሪያው ስራ ላይ ከዋለ ጀምሮ ከ3 ነጥብ 25 ትሪሊየን ብር በላይ ዝውውር ተፈጽሟል ብለዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ከግብ ለማድረስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

Exit mobile version