አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ የደቡባዊ ትብብር ድርጅት(OSC)ን ተልዕኮ ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች፡፡
እስከ ኀዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ምድረስ የሚቆየው የደቡባዊ ትብብር ድርጅት ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባዔ በድርጅቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር)÷የደቡባዊ ትብብር ድርጅት(OSC) ከተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጉልህ ውጤት እንዳስመዘገበ ገልጸው ኢትዮጵያ የድርጅቱን ተልዕኮ ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
የደቡባዊ ትብብር ድርጅት በደቡብ ደቡብ ትብብር ወሳኝ ሚና የመሆን አቅሙ ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ÷ ድርጅቱ ከሌሎች ተቋማት እና የልሕቀት ማዕከላት ጋር በትብብር መሥራት እንዳለበት ጥሪ ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ መረጃ ያመላክታል፡፡