አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ፍቃዱ በየነ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን አቅርበዋል፡፡
አምባሳደሩ በዚሁ ወቅት ከፕሬዚዳንቷ ጋር ባደረጉት ውይይት ፥ በኢትዮጵያና በታንዛኒያ መካከል የቆየ ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መኖሩን አንስተዋል፡፡
የሀገራቱ ግንኙነት በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡