አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለማስተናገድ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡
በዛሬው ዕለትም ከዝግጅት ሥራዎች ጋር በተያያዘ ከሆቴል ባለቤቶች እና ከዘርፉ አካላት ጋር መወያየታቸውን ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም ኢትዮጵያዊ ጨዋነትንና እንግዳ ተቀባይነትን አጉልተን በማሳየት በላቀ አገልግሎት ሰጪነት ማስተናገድ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረናል ብለዋል፡፡
መዲናዋን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ሥራ ይበልጥ በማጠናከር የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔን ብቻ ሳይሆን÷ ሌሎች ትላልቅ አኅጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉባዔዎች ወደ ከተማዋ እንዲመጡ ለማስቻል በቅንጅት ለመሥራት መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡