አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 150 ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት የሚያስችል የሶላር ፓምፕ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለምረቃ በቅቷል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር ) እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
ፕሮጀክቱ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና አጋሮቹ በ120 ሚሊየን ብር ወጪ በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ዙርያ ወረዳ ውስጥ መገንባቱ ተገልጿል።
ሙሉ በሙሉ በታዳሽ ሀይል የሚሰራው ይህ ፕሮጀክት በአካባቢው የመስኖ ልማትን በማሳደግ በዓመት እስከ ሶስት ጊዜ ለማምረት የሚያስችል ዕድል እንደሚፈጥር ተነግሯል።
ወደ 350 ሶላር ፓኔሎች የተተከሉለት ይህ የመስኖ ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 145 ኪሎ ዋት ማመንጨት የሚችል በመሆኑ 300 ቤተሰቦችን ተደራሽ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
በአሸናፊ ሽብሩ እና ጎህ ንጉሱ