አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቸን ሃይ በሀገራቱ መካከል በቱሪዝም ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ውይይት አደረጉ፡፡
በውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ያለውን የቱሪዝም ልውውጥ ግብይት እና ማስተዋወቅ፣ በትምህርት እና አቅም ግንባታ፣ በቱሪዝም ፕሮጀክቶች ኢንቨስትመንት፣ የቱሪስት መዳረሻዎች ልማት እና የጋራ የቱሪዝም ምርቶችን ለማልማት በሚያስችሉ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይም መክረዋል፡፡