Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፕሬዚዳንታዊ የትብብር ሜዳሊያ ተበረከተላቸው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፕሬዚዳንታዊ የትብብር ሜዳሊያ አበርክተዋል፡፡

የፕሬዚዳንታዊ የትብብር ሜዳሊያ የተበረከተላቸው ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ የሁለቱን ሀገራት የፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነት በማጠናከርና ድንበር ዘለል ወንጀሎችን በመከላከል ሂደት ላይ ባበረከቱት አስተዋፆ መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም የደቡብ ሱዳን ፖሊስ ሪፎርም ሂደትን በመደገፍ የአገልግሎቱን ከፍተኛ መኮንኖች አቅም ለመገንባት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በሰጡት የትምህርትና ስልጠና እድሎች አስተዋፅዖ መሆኑንም የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የደቡብ ሱዳን የፕሬዚዳንታዊ ጉዳዮች ሚኒስትር አምባሳደር ቾል ማውትን ጨምሮ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል መሀዲ እና የደቡብ ሱዳን ፖሊስ ኢንስፔክተር ጀነራል አተም ማሮል ተገኝተዋል፡፡

Exit mobile version