አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርሲ እና ባሌ ዞኖች በመኸር እርሻ እየተመረተ ያለው ምርት ሀገሪቱ የያዘችው የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ጉዞ እየተሳካ መሆኑን ማሳያ ነው ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ከበደ ዴሲሳ ገለጹ፡፡
ሚኒስትር ዴዔታው መንግሥት ለአርሶ አደሮች ባደረገው ድጋፍ በዞኖቹ በኩታ ገጠም እየተመረተ ያለው የስንዴና ገብስ ምርት በአርያነት የሚጠቀስ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ይህም ኢትዮጵያ የያዘችውን ሁለንተናዊ ብጽግና እያሳካች መሆኗን አመላካች ነው ማለታቸውን የአገልግሎቱ መረጃ አመላክቷል፡፡
የምግብ ሉዓላዊነት መረጋገጥ የአንድ ሀገር ሉዓላዊነት መሠረታዊ አካል መሆኑን አስገንዝበው÷ ይህን እውን ለማድረግም ውጤት ተኮር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጡ ጉዞ መንግሥት በሚሠራው ሥራ ብቻ የሚረጋገጥ ስላልሆነ÷ የግሉን ዘርፍ ጥረት፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋፋት የመገናኛ ብዙኃንን ትጋት፣ የአርሶ አደሩን እና የሕዝቡን ርብርብ ይልጋል ብለዋል፡፡