አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሚሊንየም አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘውን የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ጎብኝተዋል፡፡
ም/ጠ/ሚ ተመስገን በጉብኝታቸው በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን የሥራ ውጤት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም እንደ ሀገር ያለውን ሃብት ወደ ጥቅም ለመቀየር የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
በኤክስፖው የማዕድን አምራቾች፣ ላኪዎች፣ የክልል ማዕድን ቢሮዎችና ማህበራት ምርትና አገልግሎቶቻቸውን እያስተዋወቁ ይገኛሉ፡፡
ኤክስፖው የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ትስስር የሚፈጥሩበት ሲሆን÷ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያም ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በፍሬሕይወት ሰፊው