Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከበጋ መስኖ ልማት 13 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 ዓ.ም ከበጋ መስኖ ልማት ከ13 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ም/ሃላፊ አቶ አብዱልከሪም ሙሳ እንደገለጹት÷ በተያዘው በጀት ዓመት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በዚህ መሰረትም በበጋ መስኖ ልማት በ59 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ13 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

አነስተኛ የመስኖ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋትና በዘርፉ የታዩ ክፍተቶችን በመለየት እቅዱን ለማሳካት እየተሰራ ነው ማለታቸውንም የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

Exit mobile version