Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሞሃመድ ሳላህ ሊቨርፑል ኮንትራቱን ለማራዘም ጥያቄ ባለማቅረቡ ማዘኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብጻዊው ኮከብ ሞሃመድ ሳላህ ክለቡ ሊቨርፑል እስካሁን የኮንትራት ማራዘም ጥያቄ ባለማቅረቡ ማዘኑን አስታውቋል፡፡

የፈረኦኖቹ ንጉስ ለቢቢሲ በሰጠው አስተያየት ከሊቨርፑል ጋር ያለው የኮንትራት ውል በተያዘው ዓመት መጨረሻ እንደሚጠናቀቅ አንስቷል፡፡

ይሁን እንጂ ተጫዋቹ በሊቨርፑል እንዲቆይ ምንም አይነት የኮንትራት ማራዘሚያ ጥያቄ እንዳልቀረበለት ነው ያስረዳው፡፡

በዚህም ሁኔታዎች በሊቨርፑል ከመቆየት ይልቅ እንደምለቅ አመላካች ናቸው ብሏል ሞሃመድ ሳላህ፡፡

የ32 ዓመቱ ተጫዋች በፈረንጆቹ 2017 ከጣልያኑ ሮማ ሊቨርፑልን ከተቀላቀለ ወዲህ የክለቡ ቀዳሚ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ቀጥሏል፡፡

ተጫዋቹ በዚህ የውድድር ዓመት በሁሉም ውድድሮች 12 ግቦችን ለሊቨርፑል ማስቆጠር መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

በአንጻሩ ቢቢሲ ሊቨርፑል ተጫዋቹን ለማቆየት ፍላጎት እንዳለው ከክለቡ ታማኝ ምንጭ መረጃ ማግኘቱን አስነብቧል፡፡

ሊቨርፑል ለተጫዋቹ አስተያየት በይፋ ያለው ነገር አለመኖሩም በዘገባው ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version