አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) “የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ በሚገኘው አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ላይ የስዕል አውደ ርዕይ ለእንግዶች ክፍት ሆኗል።
የስዕል አውደ ርዕዩን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ መክፈታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በአውደ ርዕዩም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች ፣አምባሳደሮች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።