Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከ312 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አራት ወራት 312 ነጥብ 56 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የገቢ ተቋማት የአራት ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ በዚህ ወቅት÷ባለፉት አራት ወራት 311 ነጥብ 56 ቢሊየን ብር ጥቅል ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 312 ነጥብ 56 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

በዚህም የእቅዱን 100 ነጥብ 3 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው ያስረዱት፡፡

አፈጻጸሙ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ118 ነጥብ 58 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው መጠቆማቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የግብር ከፋዮችን የታክስ ሕግ-ተገዥነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ማሻሻል እንደሚገባ ጠቁመው÷ እየተስተዋለ ያለውን የታክስ ስወራና ማጭበርበር ለመፍታት መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

 

Exit mobile version