አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በመንግስት ተቀርጸው ስራ ላይ የዋሉ ፖሊሲና እስትራቴጂዎች በተጨባጭ ተግባራዊ እየሆኑ ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡
በአገልግሎቱ አስተባባሪነት ከተለያዩ መገናሃኛ ብዙሃን የተወጣጡ ጋዘጠኞች በኦሮሚያ ክልል አርሲና ባሌ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የግብርና ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በተለያዩ ወረዳዎች በሁሉም ዘርፍ የአርሶ አደሩን ሕይወት ለመለወጥ በመንግሰት ተቀርጸው ተግባራዊ እየሆኑ ካሉ አዳዲስ ኢኒሼቲቮች መካከል የግብርና ልማት ሥራ አንዱ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በአካባቢዎቹ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች መምጣታቸውን መመልከት መቻሉንም ነው አገልግሎቱ ያስታወቀው፡፡
በክላስተር የለማ የስንዴ ምርት፣ ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ፣ ዘመናዊ ቀፎን ተጠቅሞ በንብ እርባታ ላይ የሥራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች እንዲሁም በቤተሰብ ደረጃ በሌማት ትሩፋት ሥራ ኑሯቸውን እየቀየሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የመንግሰት ከሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ከበደ ዴሲሳ ÷የመግሥት ዋናው ትኩረት የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥና በቂ ምርት አምርቶ ለገበያ ማቅረብ መሆኑን አንስተዋል፡፡
እቅዱ በተጨባጭ ተግባራዊ መሆኑንና ሀገሪቱ ያላትን እምቅ አቅሞች በመለየት ወደ ተግባር በመግባት በአጭር ጊዜ አስደናቂ ለውጦች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል፡፡
የአርሶ እና አርብቶ አደሩ የሕይወት ዜይቤ እንዲ ቀየርና ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ግብርና ከባህላዊ ዘዴ ወደ ዘመናዊነት እንዲሸጋገር በማድረግ ላይ የተከናወኑ ስራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገቡ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
ይህንን ለማሳካትም መንግሰት ለአርሶ አደሩ ከሙያዊ እገዛ ጀምሮ ትራክተር፣ ኮምባይነርና የሌሎች ግብዓቶች አቅርቦትን በማመቻቸት ዘርፈ ብዙ ድጋፎች ማድረጉን ገልፀዋል፡፡
ይህንን ተከትሎም መንግስት በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የሚመረት ምርት በብዛት፣ጥራትና ፍጥነት እንዲመረት የመንግስት ቁልፍ ተግባር በመሆኑ በክላስተር፣ ጥምር ግብርናና ሌማት ትሩፋት ላይ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አመላክች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡