አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በፓፓያ ምርት ሥራ ላይ የተሰማሩ ሁሉ ጥረቶቻቸውን በእጥፍ በመጨመር እንዲተጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ጠ/ሚ ዐቢይ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ÷”ፓፓያ ለሀገር ውስጥ አቅርቦት በመዋሉ እንዲሁም ለውጭ ገበያ ባለው እምቅ አቅም የተነሳ በኢትዮጵያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ካላቸው የፍራፍሬ ዝርያዎች አንዱ ነው” ብለዋል።
የበለፀጉ የግብርና አሰራሮችን በመጠቀም አርሶአደሮች ከፍ ያለ ምርት እና የላቀ ትርፍ ሊያገኙ ይችላሉም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
በፓፓያ ምርት ሥራ ላይ የተሰማሩ ሁሉ ጥረቶቻቸውን በእጥፍ በመጨመር እንዲተጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡