አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታ የማጠቃለያ መርሃ ግብር እና የፓናል ውይይት በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ያሳለፍነው የለውጥ አመታት አግላይ እና ነጣጣይ አሰራሮች እንዲሁም ኢትዮጵያን የያዙ ኋላ ቀር አሰራሮች የተተዉበት ነው ብለዋል።
ለኢትዮጵያ ብልጽግና የሚያስፈልጉ አቃፊነትና ለውጥ አንጋቢነትን መሰረት አድርገን በብልፅግና ምእራፍ ላይ እንገኛለን ሲሉም ተናግረዋል::
በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሞገስ ባልቻ በበኩላቸው ÷ ብልጽግና ፓርቲ በሀሳብ ልዕልና ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ በማሻገር ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
በጸጋዬ ንጉስ