Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በክልሎቹ በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ውጤቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች ባለፉት የለውጥ ዓመታት ህዝብን መሠረት አድርገው በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ውጤቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፀ።

የብልጽግና ፓርቲ የተመሰረተበት 5ኛ ዓመት በዓል “የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ሀሳብ በክልሎቹ ተካሂዷል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተከናወነው የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ክልላዊ ማጠቃለያ መድረክ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን÷ ፓርቲው ለህዝብ የገባውን ቃል ዕውን ለማድረግ በተግባር እያረጋገጠ የመጣበት ወቅት ነው ብለዋል።

በክልሉ የተመዘገቡ ስኬቶችን በውጤት አጅቦ ለማስቀጠል በትኩረት መሰራት እንደሚገባ ገልጸው፤ የክልሉ መንግስት ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ መቻሉን አውስተዋል።

የተገኘውን ሠላም ለማፅናት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እና አባላት ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባልም ብለዋል።

በተመሳሳይ በጋምቤላ ክልል በተከናወነው የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ክልላዊ ማጠቃለያ መድረክ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ ኡጁሉ ኡዶል ÷ፓርቲው የክልሉ ህዝብ በሀገሩ ጉዳይ እኩል የመወሰንና የልማት ተጠቃሚ እንዲሆን ሲያነሳቸው ለነበሩት ጥያቄዎች ምላሽ ያስገኘ ነው ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያስቻለ መሆኑን የተናገሩት አቶ ኡጁሉ ፓርቲው ባለፉት የለውጥ ዓመታት ህዝብን መሠረት አድርጎ ባከናወናቸው ተግባራት የተገኙ ውጤቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

 

Exit mobile version