Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በከተማችን ከ1 ሺህ 300 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ለአገልግሎት በቅተዋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማችን በአዕምሮ እና በአካል ብቃት የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚደረጉባቸው ከ1 ሺህ 300 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ተዘጋጅተው ለአገልግሎት በቅተዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ ማለዳ የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ300 ሺሕ በላይ የከተማችን ነዋሪዎች የተሳተፉበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አከናውነናል ብለዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት ብልጽግና ፓርቲ ከተማችንን በተግባር ውብ አበባ ከማድረግ ስራው በተጨማሪ በአዕምሮ እና በአካል ብቃት የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር ሰርቷል ሲሉ ገልጸዋል።

በዚህም ነዋሪዎቻችን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉባቸው ከ1 ሺህ 300 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን አዘጋጅቶ ለአገልግሎት አብቅቷል በማለት ተናግረዋል።

Exit mobile version