አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በድሬዳዋ እና ሐረር ከተሞች በዘላቂ ቱሪዝም የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡
አምባሳደሮቹ ከጉብኝታቸው ጎን ለጎን ከድሬዳዋ እና ሐረር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጋር በኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ መምከራቸውን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
ጉብኝቱ በቀጣይ በቱሪዝም ዘርፍ ላይ መሰማራት የሚፈልጉ ዜጎቻችውን አምባሳደሮቹ እንዲጋብዙ መደላደደል ይፈጥራል ተብሏል፡፡
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ የሜክሲኮ፣ ቱርክ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ደቡብ ኮሪያ እና አውስትራሊያ አምባሳደሮች መሆናቸውም ተገልጿል፡፡