Fana: At a Speed of Life!

በአለልቱ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የሕዝብ ማመላለሻ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው።

የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሥራ ሒደት ሃላፊ አቶ ሰለሞን ዘውዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ በአደጋው እስካሁን የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በተጨማሪም በ40 ሰዎች ላይ ከባድ እና 11 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

ዛሬ ጠዋት 2:30 ላይ በተከሰተው አደጋ የተጎዱ ሰዎች በሰንዳፋ ሆስፒታል ሕክምና እተከታተሉ እንደሚገኙም አመልክተዋል።

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.