አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካብኔ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
የክልሉ ካብኔው ከተወያየባቸው አጀንዳዎች መካከል እንደሀገር ከጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ አንዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ካብኔው በሁለተኛ አጀንዳውም በክልሉ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ተግባራዊ ለማድረግ የተሻሻለው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድኅን መመሪያ ዙሪያ ተወያይቷል።
ካቢኔው ከፍለው መታከም ለማይችሉ ዜጎች በቀላሉ የሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተሻሻለውን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድኅን ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
በተጨማሪም በክልሉ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የዜጎችን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጋራ ርብርብ እንደሚጠይቅ ካቤኔው መክሯል።
ካብኔው በሌላ በኩል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የሕክምና ኦክስጂን ምርት አስተዳደር፣ ስርጭት እና አጠቃቀም ለመወሰን በመጣው መመሪያ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል፡፡