አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሄራዊ የጥራት መሠረተ ልማት ፕሮጀክት ዛሬ እንደሚመረቅ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ፕሮጀክቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት የተጀመረው መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የጥራ መንደር ካቀፋቸው ቁልፍ ተቋማት መካከልም የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ፣ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ፣ የኢትዮጵያ የሥነ ልክ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለ ሥልጣን ተጠቃሽ ናቸው።
ብሔራዊ የጥራት መሠረተ ልማት የሀገሪቱን ደረጃዎች ልማት፣ የሥነ ልክ፣ የዕውቅና አሰጣጥ፣ የተስማሚነት ግምገማ፣ የገበያ ክትትልና የጥራት ማስተዋወቅን በማጠናከር ለንግድ ድርጅቶች የሚሰጠውን የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡
በዘመናዊ መሣሪያዎች የተደገፈውና የተሻሻለ አቅም ያለው ‘የጥራት መንደር’ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ደረጃዎች ጋር በተሻለ ሁኔታ እንድትሣለጥ፣ የቴክኒክ መሰናክሎችን እንድትቀንስና በዓለም አቀፍ ንግድ ያላትን ተሳትፎ እንድታሻሽል አጋዥ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡