የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የልማት ሥራዎች እየተጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ የልማት ሥራዎች እየተጎበኙ ነው፡፡
በዚህ መሰረትም በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ እና ቢሾፍቱ ከተሞች የተለያዩ ልማት ሥራዎች ጉብኝት እየተደረገ ይገኛል።
መርሐ ግብሩ በሸገር ከተማ ገላን ጉዳ ክ/ከተማ የግብርና ልማት ኢኒሺዬቲቮችን በመጎብኘት የተጀመረ ሲሆን÷ በዚህም የእንሰሳት እርባታ፣ የዶሮና የአሳማ እርባታ እንዲሁም በመኖ ልማት የተከናወኑ ሥራዎች ተጎብኝተዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት የጎጆ ኢንዱስትሪን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወን ሲሆን÷ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ከ4 ሺህ በላይ ሼዶች እንደተገነቡ መሆኑ ተመልክቷል።
በጉብኝት መርሐ ግብሩ የፓርቲው አመራሮችና አባላት፣ የቢሮ ሃላፊዎች፣ የጨፌ ኦሮሚያ አባላት፣ አባገዳዎች፣ ሃደሲንቄዎችና የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በመራኦል ከድር