የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበጎ ፈቃድ ለተሳተፉ እውቅና ሰጡ

By Mikias Ayele

November 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ለተሳተፉ የከተማዋ ነዋሪዎች እና የብሎክ አደረጃጀቶች እውቅና ሰጡ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ሁሉ አቀፍ የህብረተሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት በሚል መሪህ ቃል የተዘጋጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ካውንስል ጉባዔ ማካሄዳቸውን ገልፀዋል፡፡

በጉባኤው ሰላምን በመጠበቅ፣ የተጓደሉ የመሰረተ ልማቶችን በመስራት እንዲሁም በሌሎች በጎ ፈቃድ እና የልማት ተግባራት ተሳትፎ ላደረጉ ነዋሪዎች እና የብሎክ አደረጃጀቶች እውቅና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር ለበርካታ አቅመ ደካማ ወገኖች መድረስ ለቻሉ ነዋሪዎች ምስጋና ያቀረቡት ከንቲባዋ÷ በቀጣይም ከተማ አስተዳደሩ ከህብረተሰቡ ጋር በትብብር መስራቱን እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል፡፡