አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው የሚሊሻ አባለት፣ የመንግስትና የግል ታጣቂዎች የድጎማና የካሳ ክፍያ መደረጉን የክልሉ ሚሊሻ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
የጽ/ቤቱ ዳይሬክተር አቶ ደምስ ስለሽ÷ ድጎማው በጦርነቱ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸውና ለተጎጂ ቤተሰቦች መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም ከ580 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ እንደ ጉዳት መጠናቸው ከ100 ሺህ እስከ 60 ሺህ ብር የሚደርስ የካሳ ድጎማ መደረጉን አስረድተዋል፡፡
ድጎማው በቀጣይ ሕግ በማስከበር ተግባር ላይ ለሚሰማሩ የጸጥታ አካላት ተልዕኳቸውን በሚገባ እንዲወጡ የሚያነሳሳ እንደሆነ መናገራቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡