የሀገር ውስጥ ዜና

መንግስት ከተሞች እንዲዘምኑ በትኩረት መስራቱን ይቀጥላል – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

By amele Demisew

November 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ከተሞች እንዲዘምኑና የቱሪስት መስህብነታቸው እንዲጨምር በትኩረት መስራቱን ይቀጥላል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

የባህር ዳር ከተማን የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ መመልከታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያመለከቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ የኮሪደር ልማት የጣና ዳር ፈርጧ ባህርዳርን ተጨማሪ ውበት የሚያላብሳት ነው ብለዋል።

በተጨማሪ ለነዋሪዎቿ፣ ቱሪስቶች እና በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ከተማዋ ለሚመጡ እንግዶች የምትመች ከተማ እንደሚያደርጋት ገልጸዋል።

በጥቂት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ የታሰበው የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ቀን ከሌት በትጋት እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ስራው በተጀመረው ትጋት እና ብርታት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን መታየቱን ጠቅሰው፤ መንግስት የከተሞች ውበት እና የተፈጥሮ ሀብት ተጠብቆ እንዲዘምኑና የቱሪስት መስህብነታቸው እንዲጨምር በትኩረት መስራቱን ይቀጥላል ብለዋል።