አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የበላይ ጠባቂ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከማህበሩ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ።
በማህበሩ ፕሬዚዳንት አበራ ቶላ የተመራው ቡድን የሰብዓዊ ድጋፍ በመስጠት ረገድ የተመዘገቡ ስኬቶችን በተመለከተ ገለጻ አድርጓል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በመላ ሀገሪቱ የሚያከናውነውን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማሻሻል የሚያስችል ለውጥ ለማድረግ የሚያከናውነውን እንቅስቃሴ በተመለከተ ማብራሪያ ማቅረቡን የማህበሩ መረጃ አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አድንቀው፤ በቀጣይ አገልግሎቱን ለማስፋት የሚያስችለውን ስትራተጂካዊ አመራር በመስጠት እና ሃብት በማሰባሰብ በገንዘብ ራሱን እንዲችል ለማድረግ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።