Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዲስ አበባ አህጉራዊ የሰላም ኮንፈረስ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አህጉራዊ የሰላም ኮንፈረንስ እንደሚካሄድ የሰላም ሚኒስቴር ገለጸ።

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ኮንፈረንሱን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ÷ በኮንፈረንሱ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች ይታደማሉ ብለዋል።

በመድረኩ በአህጉሪቱ የሰላምና የደኅንነት ጉዳይ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ጠቅሰው÷ ሀገራት በዘርፉ ያላቸውን ተሞክሮ ልምድ ይለዋወጣሉበታል ሲሉም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያም ለአፍሪካ እንዲሁም ለዓለም ሰላም ያላት አበርክቶ በመድረኩ ታቀርባለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በኮንፈረንሱ ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለአፍሪካና ለዓለም ሰላም ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገች መሆኑን የምታሳይበት ትልቅ መድረክ እንደሚሆንም ነው ያነሱት።

Exit mobile version