የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ጣሊያን በሳይበር ደኅንነት ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

By ዮሐንስ ደርበው

November 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሳይበር ኦፕሬሽን ዋና ዳይሬክቶሬት እና የጣሊያን የመከላከያ ሳይበር ክፍል በጋራ ለመስራት ተስማሙ።

የመከላከያ ሳይበር ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ኮሎኔል ሀገር አስቻለ እንዳሉት÷ ስምምነቱ በሳይበር ዘርፍ በትብብር ለመስራትና የሙያተኞችን አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡

የተቋሙን የሳይበር ጥቃት ለመከላከልና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት ስምምነቱ ጠቃሚ ነው ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

ዓለም አቀፋዊ ስጋት የሆነውን የሳይበር ጥቃት ለመከላከል ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያረጋገጡት፡፡

የጣሊያን የመከላከያ የሳይበር አዛዥ ኮሎኔል አንዲሪዮና በበኩላቸው÷ በሁለቱ ተቋማት መካከል ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም የሚችል የሰው ኃይል ለማፍራት ስምምነቱን ወደተግባር ለመለወጥ እንሠራለን ብለዋል፡፡