አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ200 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ የተለያዩ መሠረተ-ልማቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ፡፡
መሠረተ-ልማቶቹ ለሠራተኞቹ አገልግሎት እንዲውሉ ያስገነባው በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገኘው ሺንትስ ኢቲፒ ጋርመንት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በምረቃው ላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሐ ይታገሱ (ዶ/ር)፣በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጁንግ ካንግ፣ የኩባንያው ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ቻ ሚን ሆን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።