አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ይጠበቃል፡፡
ወጣቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይ መሳተፋቸው በዋናነት ከታች የተዘረዘሩትን ዋና ዋና ጉዳዮች ለመመለስ ያግዛል፡፡
- ወጣቶች በግጭቶችና አለመግባባቶች የበለጠ ተጎጅ በመሆናቸው፤
- ወጣቶች በኢትዮጵያ የስነ-ህዝብ ምጣኔ ውስጥ ከአንድ ሶስተኛ በላይ ቁጥር ያላቸው መሆኑ እና ይህም በጉዳዩ ላይ ዋነኛ ከዋኝ እንዲሆኑ ስለሚያስችላቸው፤
- ወጣቶች ሀገር ተረካቢ በመሆናቸው እና ስለነገው የሀገራቸው ጉዳይ ባለቤት በመሆናቸው፤
- ወጣቶች ለለውጥ ያላቸው ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ አዳዲስ አስተሳሰቦችን እና አመለካከቶች በምክክር ሂደቶች ለማስተናገድ ቅርብ መሆናቸው፤
- በወጣቶች ጥያቄ የነገ ሀገር ስለምትፀና የሚሉት ናቸው፡፡
ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን