አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በዩክሬን ላይ የአህጉር አቋራጭ ሚሳዔል ጥቃት መፈጸሟን ኪዬቭ አስታውቃለች፡፡
ጥቃቱ ዩክሬን በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይሁንታ በአሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎች በሩሲያ ላይ ለፈጸመችው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የአህጉር አቋራጭ ሚሳዔል ጥቃቱ የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በአይነቱ የመጀመሪያ ነው ተብሏል፡፡
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ÷ሩሲያ በዛሬው ዕለት አዲስ የሮኬት አይነት ወደ ዩክሬን ማስወንጨፏን አረጋግጠዋል፡፡
ሮኬቱም የአህጉር አቋራጭ ሚሳዔል ባህሪያት እንዳሉት ፕሬዚቱዳንቱ መናገራቸውን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል፡፡
በሌላ በኩል ሩሲያ ወደ ዩክሬን ያስወነጨፈችው የባላስቲክ ሚሳዔል ሳይሆን እንዳልቀረ ስማቸው ያልተጠቀሱ ምዕራባውያን ባለስልጣናት መግለጻቸው ተጠቁሟል፡፡