Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) የጣሊያን ድርጅቶች በጸሀይ ሀይል ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) የጣሊያን ድርጅቶች በጸሀይ ሀይል ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ አቀረቡ።

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አዉጉስቲኖ ፓሊሲ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የጣሊያን ድርጅቶች በውሃ ሀይል ማመንጫ ግድቦች ግንባታ ላይ በተለይ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና የኮይሻ የሀይል ማመንጫ ግድብ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የጣሊያን መንግስት በሀይል ማመንጫ ግንባታ ከመሳተፍ ባሻገር በውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ዘላቂና የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ስርዓት ለመዘርጋት በሚደረገው ጥረት ላይ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ንጹህ የመጠጥ ውሃ በገጠርና በከተማ ለማዳረስ በባስኬት ፈንድ ፕሮግራም ላይም በጣሊያን መንግስት በኩል አስተዋጽኦ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በሀይል ዘርፍ ላይ የሚሰሩ የጣሊያን የግሉ ዘርፍ ድርጅቶች በጸሀይ ሀይል ኢንቨስትመንት ላይ እዲሰማሩም ጥሪ ማቅረባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ጠቁሟል።

አምባሳደር አዉጉስቲኖ ፓሊሲ በበኩላቸው፤ ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ በትብብር እየሰራች እንደምትገኝ ጠቁመው በኢነርጂ፣ በውሃ ሀብትና በዋሽ ዘርፎች መንግስታቸው በትብብር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version