አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ማያ ከተማ ሀረማያ ክፍለ ከተማ በአቋራጭ መበልጸግን በማሰብ ካናቢስ የተሰኘውን የተከለከለ አደንዛዥ ዕጽ ሲያመርት የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ህብረተሰቡ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ መሰረት አቶ ጃፋር ማሃመድ የተባለው ግለሰብ በጓሮው ውስጥ ካናቢስ በማምረት ላይ ፖሊስ ባደረገው ማጣራት የደረሰበት መሆኑን የማያ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አለማየሁ ታሲሳ ለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል።
በግለሰቡ ላይ ተጨማሪ ምርመራና ማጣራት በማድረግ ጉዳዩ ለፍርድ ቤት የሚቀርብ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በከተማው ህገ ወጥ ድርጊትን ለመከላከል በተደረገው አሰሳ 120 የሺሻ ማጨሻ ቁሶች በሶስት ክፍላ ከተማ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
ህብረተሰቡ ተመሳሳይ ድርጊት ሲያይ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በቱጂ አብዲ