የሀገር ውስጥ ዜና

ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ13 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

By Shambel Mihret

November 20, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አምረፍ ሄልዝ አፍሪካ የተባለው ድርጅት ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከ13 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የጤና ስራ ለመደገፍ የሕክምና ቁሳቁስ በበቂ ሁኔታ እንደሚያስፈልግም የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ÷የሕክምና አገልግሎቱን በበቂ ሁኔታ ለመስጠትና ተደራሽ ለማድረግ የሕክምና ቁሳቁስ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በተላይም የእናቶችን ጤና ለመጠበቅ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

አምረፍ ሄልዝ አፍሪካ በኢትዮጵያ ከ22 ዓመታት በላይ የተለያዩ የጤና ስራዎችን እየደገፈ የቆየ ድርጅቱ መሆኑ የገለፁት ደግሞ በድርጅቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ምስራቅ ሞኮንን ናቸው።

ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት ትኩረት የሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ በርካታ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሆነም ገልጸዋል።

ድርጅቱ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተጨማሪም በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉ እናቶችን ጤና ለማሻሻል ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።