Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኦሮሚያ ክልል የሩዝ ሰብል ምርት መሰብሰብ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2016/17 የምርት ዘመን በመኸር ወቅት የለማ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ የሩዝ ሰብል ምርት መሰብሰብ ጀመረ፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ በጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ ተገኝተው የሩዝ ምርት ስብሰባውን አስጀምረዋል።

የቢሮ ሃላፊው በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በክልሉ ከለማው ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር በላይ የሩዝ ሰብል 63 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ከውጭ የሚገባውን የሩዝ ምርት በሀገር ውስጥ ለመተካት ጅማ ዞንን ጨምሮ በክልሉ ተስፋ ሰጪ የሩዝ ልማት ኢኒሺቲቭ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር በበኩላቸው በዞኑ 356 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሲለማ ከነበረው የሩዝ ሰብል 20 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

በተስፋሁን ከበደ እና ወርቃፈራው ያለው

Exit mobile version