Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡

በክልሉ ግብርና ቢሮ በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ትብብር በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ በኖራ የታከመ የመኸር ስንዴ ማሳ የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።

በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በአርሶ አደሩ ማሳና በማሰልጠኛ ተቋማት በምርምር በመታገዝ የተጀመረው ምርታማነትን የማሳደግ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሻሻል ለተጎዱ መሬቶች ኖራን እንደ አንድ የግብርና ግብዓት በተሟላ መልኩ መጠቀም እንደሚገባ አሳስበው÷ የኖራ አቅርቦቱን በማሳለጥ በልዩ ትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በ2016/2017 የመኸር ወቅት ከ340 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት በሰብል መሸፈኑን እና ከዚህ ውስጥም 100 ሺህ የሚጠጋው በኩታ ገጠም የለማ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ማስረሻ በላቸው በበኩላቸው፥ በምርት ዘመኑ ከ1 ሺህ 500 በላይ ሔክታር አሲዳማ አፈር በማከም ለእርሻ ስራ ምቹ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version