ዓለም አቀፉ የህፃናት ቀን በመዲናዋ እየተከበረ ነው

By Shambel Mihret

November 20, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮ የዓለም ህፃናት ቀን በዓለም ለ35ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል፡፡

ቀኑ “ህፃናት የሚሉት አላቸው እናድምጣቸው!” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በመድረኩ ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ታዳጊ ህፃናት፣ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ የህፃናት ፓርላማ ተወካዮች፣ የፌዴራል፣ የክልልና የዓለም አቀፍ ተቋማት የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መሳተፋቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።