የሀገር ውስጥ ዜና

ከ355 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

By ዮሐንስ ደርበው

November 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ከጥቅምት 29 እስከ ሕዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 355 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች መያዙን አስታወቀ፡፡

ከተያዙት ዕቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች ፣ መድኃኒት፣ የምግብ ዘይት ፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ድሬዳዋ፣ አዲስ አበባ ኤርፖርት እና ሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል፡፡