አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሊባኖስ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አሞስ ሆችስቴይን እስራኤል እና ሂዝቦላ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ለማሸማገል ቤሩት ገብተዋል፡፡
ልዩ መልዕክተኛው በቤሩት ቆይታቸው የሁለቱን ተፋላሚ ሃይሎች ባለስልጣናት እንደሚኒጋግሩ ይጠበቃል፡፡
የሊባኖስ መንግስት እና በኢራን የሚደገፈው ሂዝቦላ በዋሽንግተን የቀረበውን የተኩስ አቁም ስምምነት የጽሁፍ ምክረ ሃሳብ መቀበላቸውም ተሰምቷል፡፡
በአስራኤል በኩል በተኩስ አቁም ስምምነቱ ዙሪያ የተባለ ነገር አለመኖሩን ጠቅሶ ሬውተርስ ዘግቧል፡፡
የአሞስ ሆችስቴይን የቤሩት ቆይታም በአሜሪካ የሚመራው የዲፕሎማሲ ጥረት የሁለቱን ወገኖች ደም አፍሳሽ ግጭት መቋጫ እንደሚያበጅለት ይጠበቃል ተብሏል፡፡