የሀገር ውስጥ ዜና

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ሂደት መሳካት ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች

By Feven Bishaw

November 19, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የምክክር ሂደት እንደምታደንቅና ለሂደቱ መሳካት ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ምክትል ረዳት ፀሃፊ ቪንሴንት ስፔራ ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይቱ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር)÷ የኮሚሽኑን የእስካሁን የስራ እንቅስቃሴና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡

ቪንሴንት ስፔራ በበኩላቸው÷ ሀገራቸው ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የምክክር ሂደት እንደምታደንቅ ገልፀው፤ ለሂደቱ መሳካት ድጋፍ እንደምታደርግ ማረጋገጣቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡