አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተሿሚዎቹን የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድ ለምክር ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን ፥ ምክር ቤቱም ሹመቱን በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል ።
በዚህም ፡- 1. ወንድሙ ሴታ(ኢ/ር) – በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ 2. አቶ ታንኳይ ጆክሮዋ – የመንግስት የልማት ተቆጣጣሪ ዳይሬክተር 3. አቶ ይመር ከበደ – የአዲስ አበባ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር 4. ግዛቸው አይካ(ዶ/ር) – በአዲስ አበባ ምክርቤት የመሰረተ ልማትና መዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል ።
በመሳፍንት እያዩ