Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጉባዔውን በመጠቀም ላኪዎች የውጭ ምንዛሪ ግኝትን እንዲያሳድጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የጥራጥሬ ሰብሎችና ቅባት እህሎች ጉባዔን በመጠቀም ላኪዎች የውጭ ምንዛሪ ግኝትን እንዲያሳድጉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ፡፡

ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ በኢትዮጵያ ለ13ኛ ጊዜ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የጥራጥሬ ሰብሎችና ቅባት እህሎች ጉባዔ መከፈቱን ገልጸዋል፡፡

ጉባዔው የኢትዮጵያን ላኪዎች ከተለያዩ ዓለም ሀገራት ገዢ ኩባንያዎች ጋር ከማስተሳሰር ባለፈ የሀገራችንን ገጽታ የሚገነባ ነው ብለዋል፡፡

ይህ ጉባዔ የሚፈጥረውን መልካም ዕድል በመጠቀም በጥራጥሬና ቅባት እህሎች ላኪዎች ከነባርም ሆነ ከአዳዲስ የውጪ ሀገራት ኩባንያዎች ጋር ትስስር በማጠናከር የውጭ ምንዛሪ ግኝትን እንዲያሳድጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Exit mobile version