Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ አሶሳ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ገቡ፡፡

አቶ አደም አሶሳ የገቡት የብልጽግና ፓርቲ የ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ለመሳተፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አሶሳ ህዳሴ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

አቶ አደም በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታም ከሁሉም ክልሎች የፓርቲው ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አመራሮች ጋር በመሆን የፓርቲውን የ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም እንደሚገመግሙ ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version