አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በጉባዔው ላይ የአሥተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተገኙ ሲሆን÷ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው አስተያየትና ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያዎችን ይሰጣሉ ተብሏል፡፡
ምክር ቤቱ ዛሬ እያካሄደ ባለው ጉባዔም ከፍትሕ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ መሠረት ሰዒድ ዓሊ የተባሉ አባሉን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።