አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ወጪ የሚደረግበት የኮሪደር ልማት ሥራ በደሴ ከተማ ተጀምሯል፡፡
የኮሪደር ልማት ሥራው ከደሴ ቧንቧ ውኃ እስከ ወሎ ባሕል አምባ የሚደርስ ሲሆን÷ 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍን ተገልጿል፡፡
አጠቃላይ ስፍቱ 46 ሜትር ሲሆን÷ የእግረኛ እና የሳይክል መንገድን ጨምሮ የመዝናኛ ስፍራዎችን ያጠቃልላል ተብሏል፡፡
የኮሪደር ልማት ሥራውን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እንደሚራም ነው የተገለጸው፡፡
በከድር መሐመድ