አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በልምምድ ላይ ሳለ ባልታወቁ ሰዎች በደረሰበት ጥቃት በግራ ዓይኑ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያጋጠመው አትሌት ሰውመሆን አንተነህ ለሁለተኛ ዙር ሕክምና ወደ ሕንድ ቼናይ አቀና፡፡
አትሌቱ የሁለተኛ ዙርና የመጨረሻ የዓይን ቀዶ ጥገና ሕክምና ለማድረግ ወደ ቼናይ መጓዙን የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
ቀደም ሲል የተሳካ የመጀመሪያ ዙር የዓይን ሕክምና ማድረጉ ይታወሳል፡፡